am_tw/bible/other/lover.md

1.7 KiB

ወዳጅ (አፍቃሪ)

“ወዳጅ” የሚለው ቃል፣ “የሚወድ ሰው” ማለት ሲሆን ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው ግብረ ሥጋዊ ግንኙነት ያላቸው ሰዎችን ነው።

  • የግብረ ሥጋ ግንኙነት በባልና በሚስት መካከል ብቻ መደረግ እንዳለበት የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ወዳጅ” የሚል ቃል ጥቅም ላይ ከዋለ ብዙውን ጊዜ ከሌሎች ያላገቡ ሰዎች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት እያደረጉ ያሉ ያላገቡ ሰዎች ያመለክታል።
  • የዚህ ዐይነቱ ተገቢ ያልሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጣዖቶችን በማምለክ እስራኤል እግዚአብሔር ላይ ማመፅዋን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ውሏል። ስለዚህም፣ “ወዳጅ” የሚለው ቃል የእስራኤል ሕዝብ ያመለኳቸው ጣዖቶችን ለማመልከት በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ውሏል ማለት ነው። በእንዲህ ያሉ ዐውዶች ይህ ቃል፣ “የረከሰ ግንኙነት” ወይም፣ “የዝሙት ጓደኛሞች” ወይም፣ “ጣዖቶች” ተብሎ መተርጎምም ይችላል።
  • የገንዘብ፣ “ወዳጅ” ገንዘብ ለማግኘትና ሀብታም ለመሆን በጣም የጋለ ፍላጎት ያለው ማለት ነው።
  • ማሕልየ መሐልይ በተባለው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ፣ “ወዳጅ” የተሰኘው ቃል ቀና ወይም አዎንታዊ በሆነ መልኩ ቀርቧል።