887 B
887 B
አንበጣ
“አንበጣ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንዳንዴ እጅግ በብዛት የሚመጡ፣ ያገኙትን ሁሉ የሚበሉ በጣም አጥፊ ትልቅ በራሪ ፌንጣዎች ናቸው።
- አንበጦችና ሌሎች ፌንጣዎች ትል፣ ቀጥ ያል ክንፎችና በረጅሙ መወርወር የሚያስችሏቸው ወደ ኋላ የታጠፉ እግሮች ያሏቸው ፍጥረቶች ናቸው።
- መላው ብሉይ ኪዳን አንበጦችን የሚያቀርበው ሰብልንና እንስሳትን ለማጥፋት በብዛት እንደሚመጣ ወራሪ ነው።
- እግዚአብሔር ግብፅ ላይ ካመጣቸው አሥር መቅሠፍቶች አንዱ አንበጦች ነበር።
- መጥምቁ ዮሐንስ አንበጦችን ይመገብ እንደ ነበር አዲስ ኪዳን ያመለክታል።