1.1 KiB
1.1 KiB
ጣዖት፣ ጣዖት አምላኪ
ጣዖት እርሱን ለማምለክ ሰዎች የሚያበጁት ነገር ነው። ከአንዱ እውነተኛ አምላክ ይልቅ ለአንዳች ሌላ ነገር ክብር ሲሰጥ ያ ጣዖት አምልኮ ይባላል።
- ሰዎች የሚያመልኳቸውን አማልክት የሚወክሉ ጣዖቶች ያበጃሉ።
- እነዚህ ሐሰተኛ አማልክት ሕልውና የላቸውም፤ ከያህዌ ሌላ አምላክ የለም።
- አንዳንዴ ኀይል ያለው መስሎ እንዲታይ አጋንንት በጣዖቱ ይሠራሉ።
- ብዙውን ጊዜ ጣዖቶች ወርቅ፣ ብር፣ ናስ ወይም ውድ ዋጋ ያለውን እንጨት በመሳሰሉ ዋጋ ባላቸው ነገሮች ይሠራሉ።
- “ጣዖት አምላኪ መንግሥት” – “ጣዖት የሚያመልኩ ሰዎች መንግሥት” ወይም፣ “ ምድራዊ ነገሮችን የሚያመልክ መንግሥት” ማለት ነው።
- “የጣዖት ቅርጽ” የሚለው፣ “የጣዖት ምስል” ወይም፣ “ጣዖት” የማለት ሌላ ቃል ነው።