ቃርሚያ፣ መቃረም
ቃርሚያ አጫጆች የተዉትን ፍራ ፍሬ ወይም እህል ለመሰብሰብ እርሻ ወይም አትክልት ቦታ ውስጥ መሄድ ማለት ነው።
- መበለቶች፣ ድኾችና መጻተኞች ምግባቸውን እንዲያገኙ ኋላ ኋላ እየሄዱ እንዲቃርሙ ይፈቅድላቸውል፤ ይህም ብዙ እህል ለመሰብሰብ ያስችላቸዋል።
- ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የምትሆን፣ የሞተው ባሏ ዘመድ በሆነው ቦዔዝ እርሻ ውስጥ በነበሩት አጫጆች መካከል እንድትቃርም ተፈቅዶላት የነበረችው ሩት ናት።