am_tw/bible/other/footstool.md

2.0 KiB

የእግር መረገጫ

“የእግር መረገጫ” አንድ ሰው እግሮቹን በተለይም በሚቀመጥ ጊዜ እግሮቹን የሚያሳርፍበት ነገር ነው። መገዛትንና ዝቅ ያለ ማንነትን የሚያመለክት ትርጕም ያለው ምሳሌያው ቃልም ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሰዎች እግሮች ዝቅ ያለ ክብር ያላቸው የሰውነት ክፍሎች እንድ አሆልኑ ያስቡ ነበር። ስለሆነም፣ “የእግር መረገጫ” እግር የሚያርፍበት ከመሆኑ የተነሣ፣ “የእግር መረገጫ” ከዚያ የባሰ ዝቅ ያለ ነገር ተደርጎ ነበር የሚቆጠረው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር፣ “ጠላቶቼን የእግሮቼ መረገጫ አደርጋለሁ” ሲል በእርሱ በሚያምፁ ሰዎች ላይ ሥልታን እንዳለው፣ እንደሚቆጣጠራቸውና ጨርሶ እንደሚያሸንፋቸው ማመልከቱ ነው። ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ እስኪገዙ ድረስ በጣም ዝቅ ይላሉ ይዋረዳሉ።
  • “በእግዚአብሔር እርግ መረገጫ መስገድ” እርሱ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ እያለ ለእርሱ ለመስገድ ዝቅ ማለት ወይም መንበርከክ ማለት ነው። ይህም በድጋሚ በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ ማለትንና ለእርሱ መገዛትን ነው የሚያመለክተው።
  • የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዳዊት፣ “የእግሩ መረገጫ” ይለዋል። ይህም እርሱ በሕዝቡ ላይ ያለውን ፍጡም ሥልጣንና የበላይነት ያመለክታል። ይህ እግዚአብሔር ዙፋኑ ላይ ያለ፣ እግሮቹን መረገጫ ላይ ያደረገንጉሥ ሥዕል የሚያመልክት ሲሆን ማንኛውም ነገር ለእርሱ መገዛቱን ነው የሚያሳየው።