958 B
958 B
መብላት፣ መዋጥ፣ ጨርሶ ማቃጠል
ይህ ቃል የሚያመለክተው በአደገኛ ሁኔታ መብላትን ወይም ጨርሶ ማቃጠልን ነው።
- ጳውሎስ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ በዚህ ቃል በመጠቀም እርስ በርስ መጠፋፋት እንደሌለባቸው ማለትም በቃልም ሆነ በተግባር አንዳቸው ሌላውን ማጥቃት ወይም ማጥፋት እንደሌለባቸው አማኞችን አሰጠንቅቆ ነበር (ገላትያ 5፡15)።
- መዋጥ የሚለው ቃል ምሳሌያዊ በሆን መልኩ ጥቅም ላይ ከዋለ አገሮች እርስ በርስ እንደሚጠፋፉት ወይም እሳት ቤቶችንና ሰዎች እንደሚያቃጥለው፣ “ጨርሶ ማጥፋት” ማለት ነው።
- ይህ ቃል፣ “ሙሉ በሙሉ ማጥፋት” ወይም፣ “ጨርሶ መደምሰስ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።