1.0 KiB
1.0 KiB
መታደግ፣ ታዳጊ (የሚታደግ)
አንድን ሰው መታደግ እርሱን ማዳን ማለት ነው። ታዳጊ ከባርነት፣ ከጭቆና ወይም ከሌላ አደጋ ሰዎችን የሚታደግ ወይም ነጻ የሚያወጣ ነው።
- በብሉይ ኪዳን ዘመን እነርሱን ለማጥቃት በመጡ ሌሎች ላይ እንዲዘምቱ በማድረግ እስራኤልን የሚጠብቁና የሚመሩ ታዳጊዎች እግዚአብሔር አስነሥቶ ነበር።
- እነዚህ ታዳጊዎች፣ “መሳፍንት” ተብለውም ይጠሩ ነበር፤ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው መጽሐፈ መስፍንት እነዚህ መሳፍንቶች እስራኤልን የመሩት መቼ እንደ ነበር በዝርዝር አስፍሮአል።
- እግዚአብሔርም፣ “ታዳጊ” ተብሎአል። ከእስራኤል ታሪክ በሙሉ እንደምንመለከተው እርሱን ሕዝቡን ከጠላቶቻቸው ታድጎአቸው ወይም አድኖአቸው ነበር።