am_tw/bible/other/creation.md

1.4 KiB

መፍጠር፣ ፍጥረት፣ ፈጣሪ

“መፍጠር” አንድን ነገር ማድረግ ወይም ሕልውና እንዲኖረው ማድረግ ማለት ነው። የተፈጠረ ነገር “ፍጥረት” ይባላል። በመላው አጽናፍ ያለውን ወደ ሕልውና ያመጣ እርሱ በምሆኑ እግዚአብሔር፣ “ፈጣሪ” ይባላል።

  • ይህ ቃል እግዚአብሔር ዓለምን መፍጠሩን ለማመልከት ጥቅም ላይ ከዋለ ፍጥረትን እም ኀበ አልቦ ወይም ከምንም አስገኝቷል ማለት ነው።
  • ሰዎች ነገሮችን የሚፈጥሩት ቀድሞውኑ ከነበሩ ነገሮች ነው።
  • ሰላምን ማስገኘትን ወይም ንጹሕ ልብን መፍጠርን የመሳሰሉ ረቂቅ ነገሮችን ለማመልከት አንዳንዴ፣ “ፈጠረ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
  • “ፍጥረት” መጀመሪያ እግዚአብሔር ማንኛውንም ነገር ሲፈጥር የሆነውን የዓለምን ካለ መኖር ወደ መኖር መምጣት ሊያመለክት ይችላል። ወይም ደግም እግዚአብሔር የፈጠረውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ ሊያመለክት ይችላል። አንዳንዴ፣ “ፍጥረት” በተለይ ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎችን ያመለክታል።፥