991 B
991 B
ንቀት፣ የተናቀ
“ንቀት” አንድ ሰው ለሌላው ሰው ወይም ለሌላው ነገር ክብር መንፈጉን የሚያሳይበት መንገድ ነው። ክብር የተነፈገው፣ “የተናቀ” ይባላል።
- አንድ ሰው በግልጽ እግዚአብሔርን አለማክበሩን የሚያሳይበት መንገድ ንቀት ሲሆን፣ “ማቃለል” ወይም፣ “ማዋረድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
- “መናቅ” የአንድን ሰው ዋጋ ማሳነስ ወይም፣ ከራስ ይልቅ ሌላው ሰው ለምንም ነገር ተገቢ እንዳልሆነ መቍጠር ማለት ነው።
- ንጉሥ ዳዊት ዝሙት በማድረግና ሰውን በመግደል ኃጢአት የፈጸመ ጊዜ ዳዊት እኔን ንቆአል በማለት እግዚአብሔር ተናግሮአል። እንዲህ በማድረጉ ለእግዚአብሔር ይገባ የነበረውንክብር ነፍጎአል።