1.5 KiB
1.5 KiB
እምነት፣ መተማመን
“እምነት” እኛ “መተማመን” አንድ ነገር እውነት መሆኑንና ያም ነገር በእርግጥ የሚፈጸም መሆኑን እርግጠኛ መሆንን ያመለክታሉ። በድፍረትና በልበ ሙሉነት መንቀሳቀስንም ያመለክታሉ።
- እርሱ እንደማይዋሽና ምንጊዜም ቃሉን እንደሚጠብቅ በማወቃቸው እግዚአብሔርን በሰጣቸው የተስፋ ቃሎች አማኞች እርግጠኞች ናቸው።
- እርግጠኝነት መሠረት የሚያደርገው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩ እንኳ በእግዚአብሔር መተማመን ላይ ነው።
- ሌሎች የመጸሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች፣ “ተስፋ” በማለት የተረጎመበትን አንዳንድ ትርጕሞች፣ “እርግጠኝነት” ብለውታል፤ ይህም ያ ነገር እንደሚፈጸም በሚገባ ማወቅን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
- ብዙውን ጊዜ፣ “እምነት” የሚያመለክተው በተለይ የእግዚአብሔርን ተስፋ ቃል እውነተኛነትን፣ አንድ ቀን አማኞች ሁሉ ለዘላለም በሰማይ ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚሆኑ እርግጠኛ መሆንን ያመለክታል።
- “በእግዚአብሔር ማመን” እርሱ ቃል የገባውን ለመቀበልና ለመለማመድ በፍጹም ልብ መጠበቅ ማለት ነው።