am_tw/bible/other/conceive.md

9 lines
1.3 KiB
Markdown

# መፅነስ፣ ፅንስ
ብዙዎን ጊዜ “መፅነስ” እና፣ ፅንስ” የተሰኙ ቃሎች የሚያመለክቱት ልጅ ማርገዝን ነው። ያረገዙ እንስሳትን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።
* “ሕፃን መፅነስ” የሚለው ሐረግ “ማርገዝ” ተብሎ ወይም ይህን ለማመልከት ተቀባይነት ባለው ሌላ መንገድ መተርጎም ይችላል።
* ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያለው፣ “ፅንስ” የሚለው ቃል፣ “የእርግዝና ጅማሬ” ወይም፣ “እርጉዝ የመሆን ሂደት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
* እነዚህ ቃሎች ዐሳብን፣ ዕቅድን ወይም ተግባርን የመሳሰሉ ነገሮችን መፍጠር ወይም ማሰብንም ሊያመለክቱ ይችላሉ። እነዚህን እንደ ዐውዱ መሠረት፣ “ማሰብ” ወይም “ማቀድ” ወይም፣ “መፍጠር” ብሎ መተርጎም ይቻላል።
* አንዳንዴ ይህን ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ እንጠቀምበታለን፤ ለምሳሌ “ምሦትም ከፀነሰች በኋላ” እንደሚለው፤ እንዲህ ማለት ክፉ ምኞት አእምሮ ውስጥ ሲፈጠር ውይም ክፉ ምኞት ወድ ልብ ሲመጣ ነው።