1.1 KiB
1.1 KiB
ማጽናናት፣ አጽናኝ
“ማጽናናት” እና “አጽናኝ” የተሰኙት ቃሎች አካላዊም ይሁን ጉዳት ያደረሰባቸው ሰዎች መርዳትን፣ አይዞአችሁ ባይነትን ነው የሚያመለክተው።
- ሌሎችን የሚያጽናና ሰው፣ “አጽናኝ” ይባላል።
- ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “አጽናኝ”እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምን ያህል ቸር እና አፍቃሪ መሆኑና በመከራቸውም እንደሚረዳቸው ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል።
- በመንፈስ ቅዱስ በኩል እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዲያጽናና አዲስ ኪዳን ይናገራል። መጽናናትን የተቀበሉ መጽናናት መከራ ለደረሰባቸው ሌሎች ሰዎች ያንኑ መጽናናት መስጠት ይችላሉ።
- “የእስራኤል አጽናኝ” የተሰኘው ገለጻ ሕዝቡን ለመታደግ የሚመጣውን መሲሕ ያመለክታል።
- ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን፣ በእርሱ የሚያምኑት ሰዎችን የሚረዳ፣ “አጽናኝ” ብሎታል።