1.1 KiB
1.1 KiB
ዜና መዋዕል
“ዜና መዋዕል” የሚለው ቃል በዘመናት ውስጥ በጽሑፍ የሰፈረ ሰነድን ነው።
- ሁለት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት፣ “1ዜና መዋዕል” እና “2ዜና መዋዕል” ተብለው ተጠርተዋል።
- “ዜና መዋዕሎች” የተባሉት መጻሕፍት ከአዳም አንሥቶ የሰዎችን ስም በመዘርዘር የእስራኤልን ሕዝብ ታሪክ በከፊል አስፍረዋል።
- “1ዜና መዋዕል” የንጉሥ ሳኦልን ፍጻሜና በንጉሥ ዳዊት አገዛዝ ዘመን የተከናወኑ ሁኔታዎች አስፍሮአል።
- “2ዜና መዋዕል” የቤተ መቅደሱ መሠራትንና የሰሜኑ የእስራኤል መንግሥት ከደቡብ የይሁዳ መንግሥት መከፈሉን ጨምሮ የንጉሥ ሰሎሞንንና የበርካታ ሌሎች ነገሥታት አገዛዝ አስፍሮአል።
- 2ዜና መዋዕል የሚያበቃው የባቢሎን ምርኮ መጀመሩን በመግለጽ ነው።