1.5 KiB
1.5 KiB
ኪሩቤል፣ ኪሩብ
“ኪሩብ” እና “ኪሩቤል” በመባል በብዙ ቊጥር የሚጠሩት እግዚአብሔር የፈጠራቸው የተለዩ ዓይነት ሰማያዊ አካሎች ናቸው። ኪሩቤል ክንፎችና የእሳት ነበልባል እንዳላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል።
- ኪሩቤል የእግዚአብሔርን ክብርና ኃይል ይገልጣሉ፤ የተቀደሱ ነገሮች ጠባቂዎችም ይመስላሉ።
- አዳምና ሔዋን ኃጢአት ካደረጉ በኋላ፣ ሰዎች ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይደርሱ የእሳት ነበልባል የሆነ ሰይፍ ያላቸው ኪሩቤልን ከገነት አትክልት ቦታ አኖረ።
- ፊት ለፊት የቆሙና የኪዳኑ ታቦት፣ የስርየት መክደኛ ላይ ክንፎቻቸውን ያጋጠሙ ሁለት ኪሩቤል እንዲሠሩ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዘዘ።
- መገናኛው ድንኳን ውስጥ የነበሩ መጋረጃዎችም ላይ የኪሩቤልን ምስል በጥልፍ እንዲሠሩም ነግሮአችዋል።
- አንዳንድ ምንባቦች ውስጥ እነዚህ ፍጥረቶች አራት ፊቶች ማለትም የሰው፣ የአንበሳ፣ የበሬ እና የንስር ፌት እንዳላቸው ተገልጿል።
- አንዳንዴ ኪሩቤል መላእክት እንደ ሆነ ይታሰባል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ያንን በግልጽ አይናገርም።