1.3 KiB
1.3 KiB
ምርኮኛ፣ ምርኮ
“ምርኮና” እና፣ “ምርኮ” የተሰኙ ቃሎች መኖር በማይፈልጉበት የባዕድ አገር እንዲኖሩ ሰዎችን መያዝ ወይም ማስገደድን ያመለክታሉ።
- ከይሁዳ መንግሥት የነበሩ እስራኤላውያን ለ70 ዓመት የባቢሎን መንግሥት ምርኮኞች ሆነው ነበር።
- ዳንኤልና ነህምያ ለባቢሎን ንጉሥ ይሠሩ የነበሩ እስራኤላዊ ምርኮኞች ነበሩ።
- “ምርኮኛ መሆን” የተሰኘው ፈሊጣዊ አነጋገር ሌላውን ወገን መያዝን የሚያመልክት ሌላ አባባል ነው።
- “ምርኮኛ ትሆናላችሁ” የሚለው አባባል፣ “እንደ ምርኮኛ ለመኖር ትገደዳላችሁ” ወይም፣ “እስረኞች ሆናችሁ ወደ ሌላ አገር ትወሰዳላችሁ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
- ሐዋርያው ጳውሎስ ማንኛውንም ዐሳብ፣ “መማረክና” ለክርስቶስ እንዲታዘዝ ማድረግ እንዳለባቸው በምሳሌያዊ መልኩ ለክርስቲያኖች ይናገራል፥
- አንድ ሰው የኃጢአት ምርኮኛ መሆን ስለሚችልበት ሁኔታም ይናገራል፤ ይህም ኃጢአት፣ “ይቆጣጠረዋል” ማለት ነው።