am_tw/bible/other/bury.md

1.9 KiB

መቅበር፣ ቀበረ፣ ቀብር፣ መቀበሪያ

“መቅበር” የሞተ ሰውን አካል ጉድጓድ ውስጥ ወይም ሌላ መቀበፊያ ቦታ ውስጥ ማኖርን ያመለክታል። “ቀብር” የሚለው ቃል አንድ ነገር የመቅበር ሥራ ሲሆን፣ አንድን ነገር ለመቅበር የሚያገለግል ቦታንም ያመለክታል።

  • ብዙውን ጊዜ ሰዎች የሞተ አካልን መሬት ውስጥ በማኖርና በኋላም በአፈር በመሸፈን ይቀብራሉ።
  • አንዳንዴ የሞተው አካል ከመቀበሩ በፊት የሬሳ ሳጥን ወይም ያንን የመሰሉ ነገር ውስጥ ያኖሩታል።
  • አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ብዙውን ጊዜ የሞቱ ሰዎች ዋሻ ወይም ተመሳሳይ ቦታ ውስጥ ይቀመጡ ነበር። ኢየሱ ከሞቱ በኋላ አካሉ በጨርቅ ተጠቅልሎ ከድንጋይ በተፈለፈለ መቃብር ውስጥ ከተደረገ በኋላ መቃብሩ በትልቅ ድንጋይ ተዘጋ።
  • “የቀብር ቦታ” ወይም፣ “የቀብር ክፍል” ወይም፣ “የቀብር ዋሻ” ቃሎች በሙሉ የሞቱ አካል የሚቀመጥባቸው ቦታዎችን ያመለክታሉ።
  • ሌሎች ነገሮችም ይቀበራሉ፤ ለምሳሌ አካን ከኢያሪኮ ያለ አግባብ የወሰደውን ብርና ሌላም ነገር ቀብሮ ነበር።
  • “ፊቱን ቀበረ” የሚለው ሐረግ ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው፣ “ፊትን በእጆች መሸፈንን” ነው።
  • አንዳንዴ “መደበቅ” የሚለው ቃል አካን በኢያሪኮ የወሰደውን ነገር ሲደብቅ እንደ ሆነው፣ “መቅበር” ማለትም ይሆናል። ይህም ማለት የወሰደውን መሬት ውስጥ ቀበረው ማለት ነው።