am_tw/bible/other/breath.md

9 lines
1.3 KiB
Markdown

# እስትንፋስ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “እስትንፋስ” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ሕይወትን ለመስጠት ወይም በሕይወት መሆንን ለማመልከት በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ውሏል።
* እግዚአብሔር አዳም ውስጥ የሕይወትን እስትንፋስ፣ “እፍ” እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። አዳም ሕያው ነፍስ የሆነው ያኔ ነበር።
* ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ላይ እፍ በማለት፣ “መንፈስን ተቀበሉ” ሲላቸው ምናልባትም መንፈስ ቅዱስ ወደ እነርሱ መምጣቱን በምሳሌ ለማመልከት ቃል በቃል ከእርሱ የወጣ እስትንፋስ እፍ ብሎባቸው ይሆናል።
* “መተንፈስ” እና፣ “እፍ ማለት” የተሰኙት ቃሎች መናገርን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላሉ።
* “የእግዚአብሔር እስትንፋስ” ወይም፣ “የያህዌ እስትንፋስ” የተሰኘው ምሳሌያዊ ሐረግ ብዙውን ጊዜ ዐመፀኞችና ክፉ ሕዝቦ ላይ ያወረደውን የእግዚአብሔር ቊጣ ያመለክታል። እስትንፋሱ የኃይሉ መተላለፊያ ነው።