920 B
920 B
ገብስ
“ገብስ” እንጀራ ወይም ዳቦ ለማዘጋጀት የሚጠቅም የእህል አይነት ነው
- ገብስ ረዘም ያል አገዳ ያለው ተክል ሲሆን፥ ዘሮቹ ወይም እህሉ የሚያድገው ጫፍ ያለው ራሱ ላይ ነው።
- ገብስ ሞቃት የአየር ፀባይ ባለው አካባቢ ጥሩ ሆኖ ያድጋል፤ ስለዚህም በፀደይ ወይም በጋ ወሮች የታጨዳል
- ገብስ ሲወቃ ለምግብ የሚውለው ዘር ጥቅም ከሌለው ገለባ ይለያል
- የገብስ እህል ፍሬው ዱቄት እንዲሆን ይፈጫል፤ ከዚያም በውሃ ወይም በዘይት ይለወስና እንጀራ ወይም ዳቦ ይዘጋጃል
- ገብስ በማይታወቅበት አካባቢ፥ “ገብስ የሚባል እህል” ወይም፥ “ የገብስ እህል” ብሎ መተርጎም ይቻላል