1.1 KiB
1.1 KiB
መመደብ፥ ተመደበ
“መመደብ” ወይም፥ “መደበ” የሚለው ቃል የተወሰነ ተግባርን እንዲፈጽም አንድን ሰው መሾምን ያመለክታል
- ንጉሥ ሳኦል ከእስራኤል ወታቶች ጎበዝ የሆኑትን በወታደርነት እንዲያገለግሉ እንደሚመድባቸው ነቢዩ ሳሚኤል አመልክቶ ነበር።
- ሙሴ እያንዳንዱ የእስራኤል አሥራ ሁለት ነገድ ከነዓን ውስጥ የሚኖርበትን ምደ ድርሻ መድቦለት ነበር
- በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት አንዳንድ የእስራኤል ነገዶች በካህንነት፥ በእጅ ባልሙያነት፥ በመዘምራንነትና በግንበኝነት ይመደቡ ነበር።
- በዐውዱ መሠረት፥ “መመደብ” የሚለው ቃል፥ “መስጠት” ወይም “መሾም” ወይም “ለተወሰነ ዐይነት ተግባር መምረጥ” ብሎ መተርጎም ይቻላል
- “ተመደበ” የሚለው “ተሾመ” ወይም፥ “አንድ ሥራ ተሰጠው” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል