1.2 KiB
1.2 KiB
መሣሪያ
- “መሣሪያ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንድ ወታደር በጦርነት የሚዋጋበትንና ከጠላት ጥቃት ራሱን የሚከለክልበትን ትጥቅ ነው። መንፈሳዊ መሣሪያን ለማመልከትም በምሳሌያዊ መንገድ ጥቅም ላይ ይውላል።
- ከወታደሩ መሣሪያዎች ጥቂቶቹ የራስ ቁር፥ ጋሻ፥ ጥሩር፥ ጉልበት መሸፈኛና ሰይፍ ናቸው።
- በምሳሌያዊ መንገድ ሲጠቀምበት ቁሳዊ መሣሪያን በመንፈሳዊ ውጊያ እንዲረዳው እግዚአብሔር ለአማኝ ከሰጠው መንፈሳዊ መሣሪያ ጋር ያነጻጽረዋል
- ኅጢአትንና ሰይጣንን እንዲዋጉበት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ከሰጣቸው መንፈሳዊ መሣሪያ አንዳንዶቹ እውነት፥ ጽድቅ፥ የሰላም ወንጌል፥ እምነት፥ ድነትና መንፈስ ቅዱስ ናቸው
- ይህም፥ “የወታደሩ ማጥቂያ” ወይም “መከላከያ የጦር ልብስ” ወይም “መከለያ ሽፋን” ወይም እንዲሁ “ መሣሪያዎች” ተብሎ መተርጎም ይቻላል።