am_tw/bible/names/philippi.md

8 lines
622 B
Markdown

# ፊልጵስዩስ
ፊልጵስዩስ በጥንቷ ግሪክ ሰሜናዊ ክፍል ትገኝ የነበረች ከተማ ናት።
* ጳውሎስና ሲላስ እዚያ ለነበሩ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ለመስበክ ወደ ፊልጵስዩስ ሄደው ነበር።
* ጳውሎስና ሲላስ የታሰሩት በፊልጵስዩስ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን በተአምር ከእስር ቤት አወጣቸው።
* ጳውሎስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን የፊልጵስዩስ መልእክት የጻፈው ፊልጵስዩስ ለነበሩ ክርስቲያኖች ነበር።