ናኮር
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ናኮር ተብለው ከተጠሩ ሁለት ሰዎች አንደኛው የአብርሃም አያት ሲሆን፣ ሁለተኛው የአብርሃም ወንድም ነበር።
- የይስሐቅ ሚስት ርብቃ የአብርሃም ወንድም የናኮር ትልቋ የልጅ ልጅ ነበረች።
- “የናኮር ከተማ” የምትባል ከተማም ነበረች፤ ምናልባትም የአብርሃምን አያት ለማመልከት ይሆናል። ይህ ሐረግ፣ “ናኮር የምትባል ከተማ” ወይም፣ “ናኮር የነበረበት ከተማ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።