1.0 KiB
1.0 KiB
ባሕሩ፣ ታላቁ ባሕር፣ የምዕራብ ባሕር
መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ታላቁ ባሕር” ወይም፣ “የምዕራብ ባሕር” የሚለው በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከሚያውቁት ባሕር ትልቁ የነበረው፣ ሜዲትራንያን ባሕርን ነው።
- ታላቁ ባሕር (ሜዲትራንያን) ከእስራኤል፣ በሰሜንና በምዕራብ ከአውሮፓ፣ እና በሰሜን ከአፍሪካ ጋር ይዋሰናል።
- ብዙ አገሮችን የሚያካልል በመሆኑ በጥንት ዘመን ይህ ባሕር ለንግድና ለጉዞ በጣም ጠቃሚ ነበር። ከሌሎች አገሮች ጋር በመርከብ በቀላሉ የንግድ ልውውጥ ማድረግ በመቻላቸው በዚህ ባሕር ዳርቻ የነበሩ ከተሞችና ሰዎች በጣም ሀብታም ነበር።
- ታላቁ ባሕር የሚገኘው ከእስራኤል በስተ ምዕራብ በመሆኑ፣ “የምዕራብ ባሕር” ተብሏል።