957 B
957 B
ዮሐንስ (መጥምቁ)
ዮሐንስ የዘካርያስና የኤልሳቤጥ ልጅ ነበር። ዮሐንስ የተሰኘው ስም በጣም የተለመደ ከመሆኑ የተነሳ ሐዋርያው ዮሐንስን ከመሳሰሉ ዮሐንስ ከተባሉ ሌሎች ሰዎች እርሱን ለመለየት፣ “መጥምቁ ዮሐንስ” ተብሏል።
- ዮሐንስ በእርሱ እንደሚያምኑና መሲሑን እንዲከተሉ ሰዎችን ለማዘጋጀት እግዚአብሔር የላከው ነቢይ ነበር።
- መሲሑን ለመቀበል ዝግጁ ለመሆን ኀጢአታቸውን እንዲናዘዙ፣ ወደእግዚአብሔር እንዲመለሱና ኀጢአትን እንዲተው ዮሐንስ ለሕዝቡ ነገረ።
- በኀጢአታቸው ለመጸጸታቸውና ከኀጢአታቸው ፊታቸውን ለማዞራቸው ምልክት እንዲሆን ዮሐንስ ብዙ ሰዎችን በውሃ አጠመቀ።