830 B
830 B
ያዕቆብ (የዘብዴዎስ ልጅ)
የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብ ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነበር። ዮሐንስ የሚባል ታናሽ ወንድም የነበሩት ሲሆን፣ እርሱም ከኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነበር።
- ያዕቆብና ዮሐንስ፣ “የነጎድጓድ ልጆች” የተሰኘ መጠሪያ ነበራቸው፤ እንዲህ የተባሉት ምናልባት ቶሎ ስለሚቆጡ ሊሆን ይችላል።
- ይኸኛው ያዕቆብ፣ የያዕቆብ መልእክትን ከጻፈው የተለየ ነው። ሁለቱ የተለያዩ ሰዎች መሆናቸውን ለማመልከት አንዳንድ ቋንቋዎች ስሞቻቸውን በተለየ ሁኔታ መጻፍ የሚችሉበት መንገድ ይኖራቸዋል።