1.1 KiB
1.1 KiB
ያዕቆብ፣ እስራኤል
ያዕቆብ የይስሐቅና የርብቃ ታናሹ መንታ ልጅ ነው።
- ያዕቆብ፣ “አታላይ” ወይም፣ “አሳሳች” ማለት ነው።
- ያዕቆብ ብልጥና አታላይ ነበር። በአታላይነቱ የበኩር ልጅነትን ውርስ እና የታላቅ ወንድሙ የኤሳውን በረከት መውሰድ ችሏል።
- ኤሳው በጣም ተቆጥቶ ያዕቆብን መግደል ፈለገ፤ ስለዚህ ያዕቆብ የትውልድ ቦታውን ለቅቆ ሸሸ። በኋላ ግን ተመልሶ ከወንድሙ ጋር በሰላም ኖሮአል።
- የያዕቆብን ስም እግዚአብሔር እስራኤል ወደሚል ለወጠው፣ ያም፣ “ከእግዚአብሔር ጋር ታገለ” ማለት ነው።
- የአብርሃም ልጆች በሆኑት በይስሐቅና በልጁ በያዕቆብ በኩል እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሮቹ የገባውን ኪዳን ፈጸመ።
- ያዕቆብ አሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት። የእነርሱ ዘሮች አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ሆነዋል።