1.1 KiB
1.1 KiB
ሐማት፣ ሌቦ ሐማት
ሐማት ከምድረ ከነዓን በስተ ሰሜናዊ ሶርያ ውስጥ ትገኝ የነበረች በጣም ጠቃሚ ከተማ ናት። በዚህ ዘመን የከተማዋ ስም ሐማ ይባላል።
- “ሌቦ ሐማት” የሚለው ቃል ሐማት ከተማ አጠገብ የሚገኝ የተራራ መሻገሪያን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
- አንዳንድ ትርጕሞች “ሌቦ ሐማት” የሚለውን፣ “ወደ ሐማት መግቢያ” ብለውታል።
- “ሐማታውያን” የኖኅ ልጅ የካምና የልጅ ልጁ የከነዓን ዘሮች ናቸው።
- ንጉሥ ዳዊት የሐማት ንጉሥ የቶዑን ጠላቶች ድል በማድረጉ በሁለቱ መካከል ወዳጅነት ተመሠረተ።
- ሐማት አስፈላጊ ነገሮች የሚከማቹበት ከንጉሥ ሰሎሞን ግምጃ ቤት ከተሞች አንዷ ነበረች።
- ንጉሥ ሴዴቅያስ በንጉሥ ናቡከደነፆር የተገደለውና ንጉሥ ኢዮአካዝ በግብፃዊው ፈርዖን የተያዘው በሐማት ምድር ነበር።