ዓይንጋዲ
ዓይንጋዲ ከኢየሩሳሌም ደቡብ ምሥራቅ ይሁዳ ምድረ በዳ ላይ የምትገኝ ከተማ ስማ ነው።
- ዓይንጋዲ የሚገኘው ከጨው ባሕር ምዕራባዊ ዳርቻ ላይ ነበር።
- የስሙ ከፊል፣ “ምንጭ” ማለት ሲሆን ከከተማው ወደ ባሕሩ የሚያልፈውን የውሃ ምንጭ ለማመልከት ይሆናል።
- ዓይጋንዲ በሚያማምሩ የወይን እርሻዎቹና ምናልባትም ያለሟቋረጥ ከሚፈሰው ምንጭ የተነሣ ሌሎች ለም ቦታዎቹ ይታወቃል።
- በዓይጋንዲ ንጉሥ ሳኦል ባሳደደው ጊዜ ዳዊት ሸሽቶ የተደበቀበት ዋሻ (ምሽግ) ነበር።