አቃሮን
አቃሮን የፍልስጥኤማውያን ዋነኛ ከተማ ሲሆን የሚገኘው ከሜድትራንያን ባሕር ዘጠኝ ማይል ገባ ብሎ ያለ ቦታ ላይ ነበር።
- ቤል ዜቡል የተባለ ጣዖት ቤተ መቅደስ የሚገኘው አቃሮን ነበር።
- አንድ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ማርከው ወደ አቅሮን ወስደውት ነበር።
- በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር በአቃሮን የነበሩ ብዙ ሰዎች በበሽታ ሞቱ፣ ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ታቦቱን ወደ እስራኤል መለሱት።