ቃና
ቃና ናዝሬት በስተ ሰሜን ዘጠኝ ማይሎች ያህል ርቃ የምትገኝ ገሊላ አውራጃ ውስጥ ያለች መንደር ወይም ከተማ ነበረች።
- ቃና ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት የነበረው የናትናኤል ትውልድ ቦታ ነበረች።
- ኢየሱስ በቃና ሰርግ ላይ ተገኝቷል፤ ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ በመለወጥ የመጀመሪያ ተአምሩን ያደረገው እዚያ ነበር።
- ከዛ በኋላ አንድ ጊዜ ላይ ኢየሱስ ወደ ቃና ተመልሶ ሰመጣ ልጁን እንዲፈውስለት የጠየቀውን ከቅፍርናሆም የመጣ አንድ ሹም ጋር ተገናኘ።