am_tw/bible/names/balaam.md

10 lines
1.3 KiB
Markdown

# በለዓም
በለዓም ወደ ከነዓን ምድር ለመግባት በሰሜናዊ ሞዓብ ሰፍረው በነበረ ጊዜ እስራኤልን እንዲረግም ንጉሥ ባላቅ ቀጥሮት የነበር አረማዊ ነብይ ነበር።
* በለዓም የመጣው ከፋቱራ ከተማ ሲሆን የሚገኘው በኤፍራጥስ ወንዝ ዙሪያ ባልው አካባቢ ነበር፤ ከሞዓብ ምድር 400 ማይሎች ርቀት ላይ ይገኝ ነበር
* ሜዶናዊው ንጉሥ ባላቅ ከእስራኤል ሕዝብ ብዛትና ጥንካሬ የተነሣ ፍርሃት አድሮበት ነበር፤ ስለዚህም እነርሱን እንዲረግምለት በለዓምን ቀጠረው
* በለዓም እስራኤልን ወደነበሩበት አካባቢ በመሄድ ላይ እያለ፥ መንገዱ ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ቆሞ ስለነበር አህያው ወደፊት መሄድ አልቻለችም። እግዚአብሔር ለአህያዋ ለበለዓም የመናገር ችሎታ ሰጣት
* በለዓም እስራኤልን እንዲረግም እግዚአብሔር አልፈቀደም፤ ይልቁንም እርሱን እንዲባርክ አዘዘው
* ይሁን እንጂ፥ በኋላ ላይ በኣል ፌጎርን እንዲያመልኩ በማድረግ እስራኤል ላይ ክፉ ነገር አምጥቷል