am_tw/bible/kt/zion.md

1.6 KiB

ጽዮን፣ የጽዮን ተራራ

መጀመሪያ ላይ፣ “ጽዮን” ወይም፣ “የጽዮን ተራራ” ተብሎ ይጠራ የነበረው ንጉሥ ዳዊት ከኢያቡሳውያን የያዝሰው ምሽግ ወይም መሸሸጊያ ቦታ ስም ነበር። የኢየሩሳሌም ከተማ በተመሠረተችባቸውና የዳዊት መኖሪያ ከሆነው ኮረብቶች አንዱ ላይ ነበር የሚገኘው።

  • የጽዮን ተራራና የሞርያም ተራራ ኢየሩሳሌም የምትገኝባቸው ሁለት ኮረብቶች ናቸው። የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሠራው ሞርያም ተራራ ላይ ነበር፤ ከብዙ ዓመታት በፊት አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ለመሥዋዕት ያቀረበውም እዚያው ነበር።
  • በኋላ ላይ፣ “ጽዮን” እና፣ “የጽዮን ተራራ” የእነዚህ ተራሮችና የኢየሩሳሌም ከተማ አጠቃላይ መጠሪያ ሆነ። በኢየሩሳሌም ያለው ቤተ መቅደስ መጠሪያም ሆነ።
  • ዳዊት ጽዮንን ወይም ኢየሩሳሌምን፣ “የዳዊት ከተማ” አላት። ይህ የዳዊት ከተማ ተብሎ ከሚጠራው ዳዊት ከተወለደበት ቤተ ልሔም ከተማ የተለየ ነው።
  • እስራኤልን ወይም የእግዚአብሔር መንፈሳዊ መንግሥትን ወይም ከእግዚአብሔር ዘንድ የምትመጣው አዲሲቱ ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን በምሳሌነት ለማመልከትም፣ “ጽዮን” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።