am_tw/bible/kt/world.md

10 lines
1.3 KiB
Markdown

# ዓለም፣ ዓለማዊ
ብዙውን ጊዜ፣ “ዓለም” የሚያመለክተው አጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ሰዎች የሚኖሩበትን ማለትንን ማለትን ምድርን ነው። “ዓለማዊ” በዚህ ዓለም የሚኖሩ ሰዎችን ክፉ መንገድና አሠራር ያመለክታል።
* በጣም አጠቃላይ በሆነ መልኩ፣ “ዓለም” የሚያመለክተው ሰማያትንና ምድርን እንዲሁም በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ ነው።
* አብዛኞቹ ዐውዶች ውስጥ፣ “ዓለም” ከተባለ፣ “በዓለም ያሉ ሰዎች” ማለት ነው።
* አንዳንዴ ደግሞ በተዘዋዋሪ የሚያመለክተው በምድር የሚኖሩ መጥፎ ሰዎችን ወይም ለእግዚአብሔር የማይታዘዙ ሰዎችን ነው።
* ሐዋርያትም፣ “ዓለም” የሚለውን ቃል የተጠቀመበት በዚህ ዓለም የሚኖሩ ሰዎችን ብልሹና ራስ ወዳድ ሕይወት ለማመልከት ነበር። ይህም የሰውን ጥረት መሠረት ያደረገውንና ራሱን እንደ ጻድቅ የሚቆጥር ሃይማኖታዊ ልምምዶችን ሁሉ ያካትታል።
* እነዚህ ባሕርያት የሚታዩባቸው ሰዎችና ነገሮች፣ “ዓለማዊ” ይባላሉ።