1.4 KiB
1.4 KiB
ሥራዎች፣ ተግባሮች፣ ሥራ፣ ተግባር
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ሥራዎች”፣ “ተግባሮች” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ የዋሉት እግዚአብሔር ወይም ሰዎች ያደረጉትን በአጠቃላይ ለማሳየት ነው።
- “ሥራ” ሌሎችን ለማገልገል የተከናወነ ማንኛውንም ነገር ያመለክታል።
- “የእግዚአብሔር ሥራዎች” እና፣ “የእጆቹ ሥራ” የተሰኙት ዓለምን መፍጠሩን፣ ኀጢአተኞችን ማዳኑን፣ ለፍጥረት ሁሉ የሚያስፈልገውን መስጠቱንና አጽናፈ ዓለሙን አጽንቶ መያዝን ጨምሮ እርሱ ያደረገውን ሁሉ የሚያካትት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው።
- የሰው ሥራ ወይም ተግባር መልካም ወይም ክፉ ሊሆን ይችላል።
- አማኞች መልካም ፍሬ እንዲያፈሩ መንፈስ ቅዱስ ያስችላቸዋል፤ ይህም፣ “መልካም ፍሬ” የሚባለው ነው።
- ሰዎች የሚድኑት በመልካም ሥራቸው ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ነው።
- ሰው የሚሠራው ራሱን ለመርዳት ወይም እግዚአብሔርን ለማገልገል ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር አሁንም፣ “እየሠራ” መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል።