am_tw/bible/kt/wordofgod.md

1.7 KiB
Raw Permalink Blame History

የእግዚአብሔር ቃል፣ የያህዌ ቃል፣ የጌታ ቃል፣ ቅዱሳት መጻሕፍት

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የእግዚአብሔር ቃል” የሚባለው እግዚአብሔር ለሰዎች የተናገረው ማንኛውንም ነገር ያመለክታል። ይህም ንግግርና በጽሑፍ የሰፈረ መልእክትን ይጨምራል። ኢየሱስ ራሱ፣ “የእግዚአብሔር ቃል” ተብሏል።

  • “ቅዱሳት መጻሕፍት” “ጽሑፎች” ማለት ነው። ቃሉ የሚገኘው አዲስ ኪዳን ውስጥብቻ ሲሆን፣ የሚያመለክተው የዕብራውያንን ቅዱሳት መጻሕፍት፣ “ብሉይ ኪዳንን” ነው። እነዚህ ጽሑፎች ወደ ፊት ከብዙ ዓመታት በኋላ የሚመጡ እንዲያነባቸው በጽሑፍ የሰፈሩ የእግዚአብሔር መልእክት ናቸው።
  • “የያህዌ ቃል” እና፣ “የጌታ ቃል” የተሰኙት ተያያዥ ገለጻዎች ብዙውን ጊዜ የሚያመለክቱት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ላሉ ነቢይ ወይም ሌላ ሰው የተሰጡ በውል የሚታወቁ የእግዚአብሔር መልእክቶችን ነው።
  • አንዳንዴ የእግዚአብሔር ቃል የሚለው እንዲሁ፣ “ቃል” ወይም፣ “ቃሌ” ወይም፣ “ቃልህ” ተብሎ ተጽፏል።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ፣ “ቃል” እና፣ “የእግዚአብሔር ቃል” ተብሏል። እነዚህ መጠሪያዎች እርሱ ራሱ እግዚአብሔር በመሆኑ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ማንነት መግለጡን ያመለክታሉ።