am_tw/bible/kt/wise.md

1.5 KiB

ጠቢባን

“ጢቢባን” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የተለየ ዕውቀትና ችሎታ ያላችው ሰዎችን ለማመልከት ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ እነዚህ ሰዎች በንጉሡ አደባባይ ነበር የሚገኙት።

  • አንዳንድ ጠቢባን ከዋክብትን በማጥናት ሰማይ ላይ ያሉ ከዋክብት አቀማመጥ ትርጕም ያለው መሆኑን አመልክተዋል።
  • ብዙውን ጊዜ ጠቢባን ሕልም ለመተርጎም ይጠሩ ነበር። ዳንኤል ከንጉሥ ናቡከደነፆር ጠቢባን አንዱ ነበር፤ እግዚአብሔር የንጉሡን ሕልም መተርጎም የሚችልበት ችሎታ ሰጠው።
  • በአንዳንድ የሜድትራንያን አገሮች ጠቢባን እንደ መደበኛ ምሁራን ነበር የሚታዩት።
  • አንዳንዴ ጠቢባን ጥንቆላንና በክፉ መናፍስት ኀይል የሚደረጉ ሌሎች ነገሮችን ይለማመዱ ነበር።
  • ከአዲስ ኪዳን እንደምንመለከተው ለኢየሱስ ለመስገድ ከምሥራቅ መጥተው የነበሩት ሰዎች፣ ሰብዓ ሰገል ወይም “ጠቢባን” ይባሉ ነበር። እነዚህ ሰዎች ከዋክብትን የሚያጠኑ ኮከብ ቆጣሪዎች ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል። አንዳንዶች ዳንኤል ባቢሎን በነበረ ጊዜ ያስተማራቸው ጠቢባን ልጆች ሊሆኑ እንደሚችሉ ያስባሉ።