am_tw/bible/kt/unleavenedbread.md

1.0 KiB

ያልቦካ እንጀራ

“ያልቦካ እንጀራ” የሚያመለክተው ያለ እርሾ ወይም እንዲቦካ የሚያደርግ ሌላ ነገር ሳይገባበት የተጋገረ እንጀራን ነው። ያልቦካ ዳቦ ኩፍ አይልም፣ ስለዚህ ጠፍጣፋ ነው።

  • እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ባወጣ ጊዜ ያቦኩት ሊጥ ኩፍ እስኪል ድረስ ሳይጠብቁ በፍጥነት ግብፅን ለቅቀው እንዲወጡ ነግሮአቸው ነበር። ስለዚህ የበሉት እንጀራ ያልቦካ ነበር። ስለዚህም ይህን ጊዜ እንዲያስታውሳቸው በየዓመቱ የፋሲካን በዓል ሲያከብሩ ያልቦካ እንጀራ ይበሉ ነበር።
  • በአንዳንድ መልኩ፣ እርሾ የኀጢአት ምሳሌ በመሆኑ፣ “ያልቦካ እንጀራ” ኀጢአትን ማስወገድንና እግዚአብሔርን በሚያከብር መንገድ መኖርን ይወክላል።