1005 B
1005 B
መታመን፣ ታማኝ፣ ታማኝነት
“መታመን” አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር እውነት ወይም እምነት ሊጣልበት የሚገባ መሆኑን ያመለክታል። “ታማኝ” ሰው ትክክልና እውነት የሆነ ነገር እንደሚያደርግና እንደሚናገር እምነት ይጣልበታል።
- “መታመን” ከእምነት ጋር በጣም ይቀራረባል። አንድ ሰው ላይ ከተማመንን ቃል የገባውን እንደሚያደርግ እናምናለን።
- አንድ ሰው ላይ መታመን እርሱ ላይ መደገፍ ማለት ነው።
- በኢየሱስ፣ “መታመን” እርሱ እግዚአብሔር መሆኑንና ለኀጢአታችን ዋጋ ለመክፈል መስቀል ላይ መሞቱን፣ እርሱ እንደሚያድነን ማመን ማለት ነው።
- “የታመነ ቃል” - እውነት መሆኑ የማይጠረጠር የታመነ ንግግር ማለት ነው።