1.1 KiB
1.1 KiB
ቤተ መቅደስ
ቤተ መቅደስ እስራኤል ለጸሎትና ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ የሚሰበሰቡበት ዙሪያውን በተከበበ አደባባይ ውስጥ ያለ ሕንፃ ነው። ቤተ መቅደስ የነበረው ኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ባለው የሞሪያ ተራራ ነበር።
- አብዛኛውን ጊዜ፣ “ቤተ መቅደስ” የሚለው ቃል ዋናውን ሕንፃ የሚከብባትን አደባባዮች ጨምሮ መላውን ሕንፃ ያመለክታል። አንዳንዴ የሚያመለክተው ውስጡ የሚፈጸመውን አምልኮ ሳይሆን ሕንፃውን ብቻ ነው።
- የቤተ መቅደስ ሕንፃ ቅድስትና ቅድስተ ቅዱሳን የሚባሉ ሁለት ክፍሎች ነበሩት።
- ቤተ መቅደሱ የእርሱ ማደሪያ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ተናግሯል።
- መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ከመኖሩ የተነሣ በክርስቶስ ያመኑ ሰዎች “የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ” ተብለው ተጠርተዋል።