1.7 KiB
1.7 KiB
መገናኛ ድንኳን
መገናኛ ድንኳን እስራኤላውያን 40 ዓመት በምድረ በዳ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያመልኩበት ድንኳን መሰል ነገር ነበር
- ይህን ሁለት ክፍሎች የነበሩትን ዙሪያው ባለው አደባባይ የተከበበውን ትልቅ ድንኳን እንዴት መሥራት እንዳለባቸው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ዝርዝር መምሪያዎች ሰጥቷቸዋል
- እስራኤላውያን ወደ ሌላ ቦታ በተንቀሳቅሱ ጊዜ ሁሉ ካህናቱ የመገናኛውን ድንኳን በማፍረስ እስከ ቀጣዩ ሰፈር ድረስ ይሸከሙታል። ከዚያም አዲሱ ሰፈራቸው መካከል የተክሉታል
- የመገናኛው ድንኳን ከጨርቅ፣ ከፍየል ጠጉርና ከእንስሳት ቆዳ የተሠሩ መጋረጃዎች በተሰቀሉበት የእንጨት ማዕቀፍ የተሠራ ነበር። ዙሪያው ያለው አደባባይም በሌሎች መጋረጃዎች የተከበበ ነበር
- የመገናኛው ድንኳን ሁለቱ ክፍሎች ቅድስት (የዕጣኑ መሠዊያ ያለበት) እና ቅድስተ ቅዱሳን (የቃል ኪዳኑ ታቦት ያለበት) ናቸው
- የመገናኛው ድንኳን አደባባይ ለመሥዋዕት የቀረቡ እንስሳት የሚቃጠሉበት መሠዊያና ለሃይማኖትዊ ሥርዓቱ የሚታጠቡበት ልዩ መታጠቢያ ክፍል ነበረው
- በኢየሩሳሌም የነበረው የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ከተሥራ በኋላ እስራኤላውያን መገናኛው ድንኳን ጥቅም ላይ መዋሉ ቀረ