am_tw/bible/kt/son.md

11 lines
1.9 KiB
Markdown

# ልጅ፣ የ. . . ልጅ
“ልጅ” የሚለው ቃል ከወላጆቹ ጋር ካለው ግንኙነት አንፃር ትንሽ ልጅን ወይም ሰውን ያመለክታል። የአንድ ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ወይም እንደ ልጅ የተቀበለውን ሰው ያመለክታል
* ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ልጅ” የሚለው ቃል የልጅ ልጅ ወይም የልጅ ልጅ ልጅ የሆነ ማንኛውንም ወንድ ያመለክታል
* “ልጄ” የሚለው ቃል ሕፃን ልጅ ወይም ጎልማሳ በፍቅር የሚጠራበት ቃል ሊሆን ይችላል
* አዲስ ኪዳን ውስጥ በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎችን ለማመልከት፣ “የእግዚአብሔር ልጆች” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል
* “የ. . . ልጅ” የሚለው ቃል፣ ብዙ ጊዜ “የእርሱ ባሕርይ ያለው” የሚል ትርጉም ያለው ምሳሌያዊ አነጋገር ነው። ለምሳሌ፣ “የብርሃን ልጆች” ፣ “የመታዘዝ ልጆች” ፣ “የሰላም ልጆች” እና፣ “የነጎድጓድ ልጆች” እንደተሰኙት
* “የ. . . ልጅ” የዚያን ሰው አባት ለማመልከትም በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ውሏል። ይህ ሐረግ የትውልድ ቆጠራን አስመልክቶ በተለያየ ቦታ ጥቅም ላይ ውሏል
* የአባቱን ስም ለማመልከት “የ. . . ልጅ” የሚለው ሐረግ ተደጋግሞ ጥቅም ላይ ከዋለ ተመሳሳይ ስም ያላቸውን ሰዎች ለመለየት ይጠቅማል። ለምሳሌ፣ 1ነገሥት 4 ላይ እንዳለው “የሳዶቅ ልጅ አዛርያስ” እና፣ “የናታን ልጅ አዛርያስ” ወይም 2ነገሥት 15 ላይ፣ “የአማስያ ልጅ አዛርያስ” የተባሉ ሦስት የተለያዩ ሰዎች አሉ