am_tw/bible/kt/sin.md

1.4 KiB

ኅጢአት፣ ኅጥእ፣ ኅጢአተኛ፣ ኅጢአት ማድረግ

“ኅጢአት” የሚለው ቃል ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የሚደረግ ተግባርን፣ ሐሳብንና ቃልን ያመለክታል። እግዚአብሔር ያዘዘውን አለማድረግም ኅጢአት ነው

  • ኅጢአት ሌሎች ሰዎች ባያውቁ እንኳ ማንኛውንም እና የምናደርገውን ለእግዚአብሔር የማይገዛና እርሱን ደስ የሚያሰኝ ነገር ሁሉ ይጨምራል
  • ለእግዚአብሔር ፈቃድ የማይገዛ ሐሳብና ተግባር ሁሉ፣ “ኅጢእ” ነው
  • አዳም ኅጢአት በመድረጉ የሰው ልጆች ሁሉ እነርሱን ከሚቆጣጠር ኅጥእ ዝንባሌ ጋር ተወልደዋል
  • “ኅጢአተኛ” ኅጢአት የሚያደርግ ሰው ነው፤ ሰዎች ሁሉ ኅጢአተኞች ናቸው
  • አንዳንዴ ፈሪሳዊያንን የመሳሰሉ የሃይማኖት ሰዎች ሕጉንና እነርሱ መጠበቅ አለባቸው የሚሉትን ነገር የማይጠብቁ ሰዎች ለማመልከት “ኅጢአተኛ” በተሰኘው ቃል ይጠቀማሉ
  • ከሌሎች የከፋ ኅጢአተኞች የሆኑ ሰዎችን ለማመልከት፣ “ኅጢአተኞች” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል። ለምሳሌ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች፣ በዚህ ቃል ተጠርተዋል