am_tw/bible/kt/satan.md

873 B
Raw Permalink Blame History

ሰይጣን፣ ዲያብሎስ፣ ክፉው

ዲያብሎስ እግዚአብሔር የፈጠረው መንፈሳዊ አካል ነበር፤ በእግዚአብሔር መማመፁ የእግዚአብሔር ጠላት ሆነ። ዲያብሎስ፣ “ሰይጣን” እና፣ “ክፉው” ተብሎ ይጠራል

  • የእግዚአብሔርን ቦታ ለመውሰድና እንደ እግዚአብሔር መመለክ በመፈለጉ ዲያብሎስ እግዚአብሔርንና እርሱ የፈጠረውን ሁሉ ይጠላል
  • ሰይጣን በእግዚአብሔር እንዲያምፁ ሰዎችን ይፈታተናል
  • ሕዝቡን ከሰይጣን ቁጥጥር ለማዳን እግዚአብሔር ልጁ ኢየሱስን ላከ
  • “ሰይጣን” “ጠላት” ወይም፣ “ባላጋራ” ማለት ነው
  • “ዲያብሎስ” “ከሳሽ” ማለት ነው