am_tw/bible/kt/righteous.md

1.1 KiB

ጻድቅ፣ ጽድቅ

“ጻድቅ” እና፣ “ጽድቅ” የእግዚአብሔር ፍጹም መልካምነት፣ ፍትሕ፣ ታማኝነትና ፍቅር ያመለክታል። እግዚአብሔር ጻድቅ ስለሆነ ኀጢአት ላይ መፍረድ አለበት።

  • አብዛኛውን ጊዜ ይህ ቃል ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና በግብረ ገባዊ ሕይወቱ መልካም የሆነ ሰውንም ሊያመለክት ይችላል። ይሁን እንጂ፣ ሰዎች ሁሉ ኀጢአት በማድረጋቸው፣ ከእግዚአብሔር በቀር ፍጹም ጻድቅ የሆነ ማንም የለም።
  • መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ጻድቃን” በማለት በሚጠራቸው ስሞች ዝርዝር ውስጥ ኖኅ፣ ኢዮብ፣ አብርሃም፣ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ይገኛሉ።
  • እርሱ እንዲያድናቸው ሰዎች በኢየሱስ ሲያምኑ፣ እግዚአብሔር ከኀጢአታቸው ያነጻቸዋል፤ ከኢየሱስ ጽድቅ የተነሣ እነርሱም ጻድቃን መሆናቸውንም ይናገርላቸዋል።