ትንሣኤ
“ትንሣኤ” ከሞት በኋላ ተመልሶ ወደ ሕይወት መምጣት ነው።
- አንድን ሰው ማስነሣት ያንን ሰው እንደ ገና ወደ ሕይወት ማምጣት ማለት ነው። ያን የማድረግ ኀይል ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
- ብዙውን ጊዜ፣ “ትንሣኤ” የሚያመለክተው ከሞት በኋላ ኢየሱስ ወደ ሕይወት መመለሱን ነው።
- ኢየሱስ፣ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ” ሲል፣ እርሱ የትንሣኤ ምንጭ መሆኑንና ሰዎችን መልሶ ወደ ሕይወት የሚያመጣ መሆኑን መናገሩ ነበር።