am_tw/bible/kt/redeem.md

1.2 KiB

መዋጀት

“መዋጀት” የሚለው ቃል በሌሎች ተወስዶ የነበረ ነገርን በመግዛት የራስ ማድረግ ማለት ነው።

  • ሰዎችን ወይም ነገሮችን እንዴት እንደሚዋጁ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሕግ ሰጥቷል።
  • ለምሳሌ፣ ለእርሱ ዋጋ በመክፈል ባርያውን፣ “መዋጀት” ይቻላል። “ቤዛ” የሚለውም ቃል የሚያመለክተው ይህንኑ ነው።
  • የአንድ ሰው ርስት ከተሰጠ፣ ርስቱ ከቤተ ሰብ እንዳይወጣ የዚሃ ሰው ዘመድ፣ “ይዋጀዋል” ወይም፣ “እንደ ገና ይገዛዋል።”
  • እንዲህ ያሉት አሠራሮች የኀጢአት ባርያ የነበሩ ሰዎችን እግዚአብሔር በእንዴት ያለ ሁኔታ እንደ “ዋጀ” ያሳያሉ። መስቀል ላይ በሞተ ጊዜ ኢየሱስ የሰው ልጆችን ኀቲአት ዋጋ ከፈለ፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ሁሉ “ይዋጃቸዋል።” እግዚአብሔር የዋጃቸው ከኀጢአትና ከሚያስከትለው ቅጣት ነጻ ናቸው።