am_tw/bible/kt/passover.md

1.3 KiB

ፋሲካ (ማለፍ)

ፋሲክ እግዚአብሔር አባቶቻቸው እስራኤላውያንን እንዴት ከግብፅ ባርነት እንዳዳናቸው ለማሰብ አይሁድ በየዓመቱ የሚያከብሩት ሃይማኖታዊ በዓል ስም ነው።

  • የዚህ በዓል ስም የመጣው፣ የግብፃውያንን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ሲገድል እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን ቤት፣ “አለፈ” ልጆቻቸውንም አልገደልም ከሚለው ታሪክ ነው።
  • የፋሲካ አከባበር ምንም ጉድለት የሌለበት በግ በማረድ፣ ሥጋውን ጠብሶ ልዩ ዓይነት ምግብ ማዘጋጀትንና እርሾ የሌለበት እንጀራ መብላትንም ይጨምራል። ይህ ምግብ ከግብፅ ከመውጣታቸው በፊት በነበረው ሌሊት እስራኤላውያን ተመግበውት ስለ ነበረው ምግብ ያስታውሳቸዋል።
  • እግዚአብሔር ቤቶቻቸውን “እንዳለፈና” በእንዴት ዓይነት ሁኔታ ከግብፅ ባርነት እንዳዳናቸው እንዲያስታውሱ በየዓመቱ ፋሲካን እንዲያከብሩ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል።