am_tw/bible/kt/justice.md

1.3 KiB

ትክክል፣ ፍትሕ፣ በፍትሕ

እነዚህ ቃሎች የሚያመለክቱት በእግዝአብሔር ቃል መሠረት ሰዎችን በአግባቡ መያዝን ወይም ማስተናገድን ነው። ትክክል የሆነውን የእግዚአብሔር መስፈርት የሚያንጸባርቁ የሰው ልጆች ሕጎችም ፍትሕ ይባላሉ።

  • “ፍትሕ ማድረግ” ለሌሎች ቀና የሆነውን ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ማለት ነው። ከግብረ ገባዊ ይዘቱ አንጻር በእግዚአብሔር ፊት ቅንነትና ታማኝነት ያለበት ነገር ማድረግንም ይጨምራል።
  • “በፍትሕ” መፍረድ በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት ትክክል፣ መልካምና አግባብ በሆነ ሁኔታ ሰዎችን ማስተናገድ ማለት ነው።
  • “ፍትሕ” ማግኘት በሕጉ መሠረት በአግባቡ መስተናገድ፣ ከሕጉ ከለላ ማግኘት ወይም ሕጉን በመተላለፍ መቀጣት ማለት ነው።
  • አንዳንዴ፣ “ትክክል” የሚለው ቃል ሰፋ ባለ መልኩ፣ “ጻድቅ” ወይም፣ “የእግዚአብሔርን ሕግ መከተል” የሚል ትርጉም ይኖረዋል።