am_tw/bible/kt/inherit.md

3.0 KiB

መውረስ፣ ውርስ፣ መብት፣ ወራሽ

“መውረስ” እና፣ “ውርስ” ከእነርሱ ጋር ካለ የተለየ መቀራረብ የተነሣ ከወላጆቹ ወይም ከሌሎች ጠቃሚ ነገር መቀበል ማለት ነው። ያንን ውርስ የሚቀበል ወራሽ ይባላል።

  • በውርስ የሚገኙ ቁሳዊ ነገሮችን ገንዘብ፣ መሬት ወይ ሌሎች ንብረቶች ሊሆኑ ይችላሉ።
  • በኢየሱስ ለሚያምኑ ሁሉ እግዚአብሔር ለሰዎች የሚሰጠው ማንኛውም መንፈሳዊ ውርስ በዚህ ሕይወትም ሆነ ከእርሱ ጋር ለዘላለም ሕይወት የሚጠቅሙ በረከቶችን ሁሉ ያካትታል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ የእርሱ ሕዝብ የእግዚአብሔር ርስት መሆናቸውንም ይናገራል፤ ይህም ማለት እነርሱ የእርሱ ናቸው፤ በእርሱ ዘንድ እጅግ የከበሩ ናቸው ማለት ነው።
  • “መብት” ከውርስ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፣ አንድ ሰው ከወላጆቹ ወይም ከእግዚአብሔር የሚያገናኛቸው ቁሳዊ ያልሆኑ በረከቶችንና ባሕርያትን ብቻ ያመለክታል።
  • ምድረ ከነዓንን እንደሚወርሱና ለዘላለም የእነርሱ እንደሚሆን ለአብርሃምና ለዘሮቹ እግዚአብሔር ቃል ገብቷል።
  • የእግዚአብሔር የሆኑ ሕዝቡ፣ “ምድሪቱን ስለሚወርሱበት ሁኔታ” የሚያመለክት ምሳሌያዊ ወይም መንፈሳዊ አነጋገርም አለ። ይህም ማለት በቁሳዊም ሆነ በመንፈሳዊ ደረጃ ይበለጽጋሉ፣ በእግዚአብሔር ይባረካሉ ማለት ነው።
  • በኢየሱስ የሚያምኑ፣ “የድነት ወራሾች” እና፣ “የዘላለም ሕይወት ወራሾች” እንደሚሆኑ በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ተስፋ ቃል ሰጥቷል። “የእግዚአብሔር መንግሥት ወራሾች” ተብሎም ተገልጿል። ይህ ለዘላለም የሚኖር መንፈሳዊ ርስት ነው።
  • እነዚህን ቃሎች በተመለከተ ሌሎች ምሳሌያዊ ትርጉሞችም ይኖራሉ፤
  • አስተዋዮች፣ “ክብር እንደሚወርሱ” እና፣ ጻድቃን፣ “ መልካም ነገሮችን እንደሚወርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
  • “የተስፋው ወራሽ” ማለት እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንደሚሰጥ ቃል የገባው መልካም ነገርን ሁሉ መቀበል ማለት ነው።
  • ሞኞችና የማይታዘዙ ሰዎች፣ “ነፋስን እንደሚወርሱ” ወይም፣ “ከንቱነትን እንደሚወርሱ” ለማመልከት ይህ ቃል አሉታዊ በሆነ መልኩም ጥቅም ላይ የዋለበት ሁኔታም አለ። ይህም ማለት ቅጣትንነ ከንቱ አኗኗርን ጭምሮ ኀጢአተኛ ተግባራቸው የሚያስከትለውን ሁሉ ይቀበላሉ ማለት ነው።