am_tw/bible/kt/imageofgod.md

1.2 KiB

የእግዚአብሔር አምሳል፣ ምስል

“አምሳያ” የሚለው ሌላውን የሚመስል፣ በጸባይም ሆነ በጥንተ ተፈጥሮው ሌላውን የመሰለ ማለት ነው። “የእግዚአብሔር አምሳል” የሚለው ሐረግ እንደ አውዱ ሁኔታ በተለያየ መንገድ ጥቅም ላይ ይውላል።

  • ጊዜ ሲጀመር እግዚአብሔር የሰው ልጆችን፣ “በራሱ አምሳል” ማለትም፣ “እርሱን አስመስሎ” ፈጠረ። ይህም ማለት የሰው ልጆች ምክንያታዊነትና ከሌሎች ጋር ተራክቦ የማድረግ ችሎታና ለዘላለም የሚኖር መንፈስ አላቸው ማለት ነው።
  • የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ፣ “የእግዚአብሔር ምሳሌ” መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል፤ ያም ማለት እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ከሰው ልጆች በተለየ መልኩ ኢየሱስ ፍጡር አይደለም። እስከዘላለም የእግዚአብሔር አብ ባሕርያት ስላሉት እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ሁሌም መለኮታዊ ባሕርያት አሉት።